የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2017 በጀት አመት ባደረገው የስራ አፈፃፀም ግምገማ የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ከተሞችና ክልሎች እዉቅና ሰጥቷል።
የአዲስ አበባ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮም ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተወዳድሮ አንደኛ በመዉጣት ሽልማት ተበርክቶለታል።
ቢሮው ከኢፌደሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የሜዳሊያ: የዋንጫ: የኮምፒዩተር እና የላፕቶፕ ሽልማት ተበርክቶለታል::
ሽልማቱን የተቀበሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ለቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች፣ ለክፍለ ከተማ አመራሮችና ሰራተኞች በሙሉ ምስጋና አድርሰዋል።
አቶ ጃንጥራር አክለውም: የእውቅና ሽልማቱ በ2018 የተሻለ ለመስራት የሚያነሳሳ ነው ብለዋል::