አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሃገራዊ የምክክር ሂደትን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ላበረከተዉ የጎላ አስተዋጽኦ እዉቅና አገኘ

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሃገራዊ የምክክር ሂደትን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ላበረከተዉ የጎላ አስተዋጽኦ እዉቅና አገኘ

AMN ሃምሌ 26/2017

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሃገራዊ የምክክር ሂደትን ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ ላበረከተዉ የጎላ አስተዋጽኦ ከሃገራዊ የምክክር ኮሚሽን እዉቅና አገኘ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመገናኛ ብዙሃን እና ከኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት የሚያጠናክር የውይይትና ምስጋና መርሃግብር በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕሮፌሰር) መገናኛ ብዙሃንና የኮሙኒኬሽን ተቋማት የምክክሩን ሂደት ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ለሰሩት ስራ በኮሚሽኑ ስም አመስግነዋል፡፡

በቀጣይ ሀገራዊ ምክክሩ ከመካሄዱ በፊት ሰፊ የሚድያና ኮሙኒኬሽን ስራ በመስራት በሂደቱ የላቀ የማህበረሰብ ተሳትፎ እንዲኖር የተለመደ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ መድረክ የምክክሩን ሂደት ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት ዕዉቅና የተሰጠ ሲሆን አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የምስጋና ምስክር ወረቀት ከኮሚሽኑ ተበርክቶለታል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በቴሌቭዥን: በFM 96.3 : በአዲስ ልሳን ጋዜጣና በዲጂታል ሚዲያዉ የሃገራዊ ምክክር ሂደቱን ለህዝብ ተደራሽ በማድረጉና ማህበረሰቡ ስለ ሃገራዊ ምክክሩ ያለዉን ግንዛቤ ለማሳደግ ባደረገዉ የጎላ አስተዋጽኦ ነዉ ከኮሚሽኑ እዉቅና ያገኘዉ።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review