የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር የብልፅግና ጉዟችንን የሚያሳካ የብረት መንገድ ነው ሲሉ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናገሩ

You are currently viewing የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር የብልፅግና ጉዟችንን የሚያሳካ የብረት መንገድ ነው ሲሉ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናገሩ
  • Post category:ልማት

AMN- ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም‎

የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ሸቀጦችን የሚሸከም ብቻ ሳይሆን የብልፅግና ጉዟችንን የሚያሳካ የብረት መንገድ ነው ሲሉ የባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልጸዋል።

የኢትዮ- ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ባለፈው አንድ ዓመት ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ የሠራተኞች ቀን መርሐ-ግብር አከናውኗል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ፣ የኢትዮ-ጂቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና የድርጅቱ አመራርና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

ኢንጅነር ታከለ ኡማ፣ ቀደምት አያቶቻችን ከዓድዋ ድል ማግስት ኢትዮጵያን ከተቀረው ዓለም ለማስተሳሰር እና የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳለጥ የባቡር መስመር መስራታቸውን አውስተዋል።

የባቡር አገልግሎቱ የኢትዮጵያና ጂቡቲ የወንድማማችነት መገለጫና ሀውልት ነው ብለዋል።

ሆኖም የባቡር አገልግሎቱ ከምስረታው ጀምሮ እና ዳግም አገልግሎት ከጀመረ ወዲህም በተለያዩ ውጫዊና ውስጣዊ ጫናዎች ሳቢያ ሲወጣ ሲወርድ መቆየቱን ጠቅሰው፣ ዕድገቱን ለማስቀጠል ሪፎርም እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያና በጂቡቲ ባለሙያዎች እንዲመራ በማድረግ እና ዘመኑን በዋጀ የአሠራር ማሻሻያ ተጨባጭ ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸዋል።

የባቡር መስመሩ የኢትዮጵያን ሸቀጥ ብቻ ሳይሆን ተስፋዋን እና ራዕይዋን ይዞ የሚጓዝ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለላቀ ስኬት እስከ 2020 ዓ.ም የሚተገበር የሦስት ዓመት ፕሮጀክት ይፋ መደረጉን አመላክተዋል።

የብረት መንገዱ ኢትዮጵያንና ጂቡቲን ከዓለም የሚያገናኝ የብልፅግና መስመር ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ፣ የማይላላ የማስተሳሰሪያ ፕሮጀክትነቱ በላቀ ውጤት ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review