ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀመረ

You are currently viewing ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀመረ

AMN ሐምሌ 28/2017

”ሃይማኖቶች ለሰላም፣ለአንድነት እና ለአብሮነት” በሚል መሪ ሃሳብ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት 4ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሐረሪ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የሰላም ጉባዔ ”ሃይማኖቶች ለሰላም፣ለአንድነት እና ለአብሮነት” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በጉባዔው ላይ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር ፣ የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሓፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፣ የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂ አባቶች ተወካዮች፣ ከተለያዩ ክልሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ የስራ ኃላፊዎች ታድመዋል።

በዚሁ ሀገር አቀፍ ጉባዔ ላይ 300 የሚሆኑ የሁሉም ክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች የሚታደሙ ሲሆን በኮንፍረንሱ ላይ ሁለት ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል።

ከዚህ በተጨማሪ ተሳታፊዎቹ በሐረሪ ክልል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላና በክልሉ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review