በሩቅ ምሥራቃዊ ሩሲያ ውስጥ የፈነዳው እሳተ ገሞራ፣ ከ500 ዓመታት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ይህም ካለፈው ሳምንት ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ተናግረዋል ።
በካምቻትካ የሚገኘው የክራሼኒኒኒኮቭ እሳተ ገሞራ፣ በአንድ ሌሊት እስከ ስድስት ኪሎ ሜትር ከፍታ ያለው አመድ ከከርሰምድር መውጣቱ ታውቋል።
ሁኔታውን በተመለከተ የሩሲያ የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ምንም አይነት ስጋት የለም ሲል አስታውቋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ፣ በሦስት ደሴቶች አካባቢ የሱናሚ ማስጠንቀቂያ ማስከተሉን ቢቢሲ ዘግቧል።
ክስተቱ ባለፈው ሳምንት ተመሳሳይ ቦታ ላይ ከደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ፈረንሳይ ፣ ፖሊኔዥያ እና ቺሊ ድረስ የሱናሚ ማስጠንቀቂያዎችን አስከትሏል ተብሏል።
ይህ ክስተት በአከባቢው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ማድረጉ ታውቋል።
በብርሃኑ ወርቅነህ