የቻይናው አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪ አቅራቢ ዊ ራይድ፤ በ6 የዓለም ሀገራት በአሽከርካሪ አልባ ታክሲዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ተቀባይነት ያገኘ የመጀመሪያው ኩባንያ ሆኗል።
ሳዑዲ እነዚህን አሽከርካሪ አልባ ታክሲዎች ለማስገባት የመጀመሪያዋ ስትሆን፣ ከኡበር እና ኤ አይ ድራይቨር ከተሰኙ ተቋማት ጋር በማቀናጀት በሀገሪቱ አገልግሎት እንደሚሰጥ ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።
የ ዊ ራይድ አሽከርካሪ አልባ አገልግሎት ከሳዑዲ አረቢያ የ2030 የስማርት ከተማ ራዕይ ጋር አብሮ እንደሚሄድ ተዘግቧል።
ከአሽከርካሪ አልባዎቹ ሮቦ ታክሲዎች በተጨማሪ ሮቦ አውቶቡሶች እና ሌሎችንም አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን አምርቷል።
ኩባንያው ከሳዑዲ አረቢያ በተጨማሪም በቻይና፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ሲንጋፖር፣ ፈረንሳይ እና አሜሪካ አገልግሎት ለመስጠት ፍቃድ ማግኘቱ ተገልጿል።
በሊያት ካሳሁን