የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ዊትኮፍ ወደ ሩሲያ ሊያቀኑ ነው

You are currently viewing የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ዊትኮፍ ወደ ሩሲያ ሊያቀኑ ነው

AMN- ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ያስቀመጡት የማዕቀብ ቀነ-ገደብ ከመድረሱ በፊት ልዩ መልእክተኛቸው ስቲቭ ዊትኮፍ ሩሲያን እንደሚጎበኙ አስታውቀዋል።

የአሜሪካ 2 የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከቦች በቀጣናው ተሰማርተዋል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ሰርጓጅ መርከቦቹ በኒውክሌር የጎለበቱ አሊያም ኒውክሌር የታጠቁ ስለመሆናቸውም ሆነ ስለተሰማሩበት ትክክለኛ ቦታ ግልፅ አላደረጉም።

ኒውክሌር ነክ ማስጠንቀቂያው የተሰነዘረው፣ የተቀመጠው ቀነ ገደብ በመጪው ሳምንት መጨረሻ የሚያበቃ መሆኑን ተከትሎ እንደሆነ አር ቲ ኢ አስነብቧል።

ሩሲያ ወደ ሰላም ስምምነቱ እስካልመጣች ድረስ በተዘዋዋሪ ሊጎዳት የሚችል፣ የንግድ አጋሮቿ የሆኑትን ቻይና እና ህንድን ኢላማ ያደረገ ታሪፍ በሃገራቱ ሊጣል እንደሚችል ዶናልድ ትራምፕ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

በሚቀጥለው ሳምንት አጋማሽ የሚጠበቀው የዊትኮፍ ጉዞ ለተኩስ አቁሙ የአሜሪካ የመጨረሻው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሊሆን እንደሚችል ዘገባው አመላክቷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review