በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል የቀድሞ ባለስልጣናት ትራምፕ የጋዛን ጦርነት እንዲያስቆሙ የተማፅኖ ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል የቀድሞ ባለስልጣናት ትራምፕ የጋዛን ጦርነት እንዲያስቆሙ የተማፅኖ ጥሪ አቀረቡ

AMN – ሃምሌ 29/2017 ዓ.ም

በመቶዎች የሚቆጠሩ የእስራኤል የቀድሞ ባለስልጣናት ትራምፕ የጋዛን ጦርነት እንዲያስቆሙ የተማፅኖ ጥሪ አቀረቡ።

የእስራኤል የቀድሞ የደህንነት ኤጀንሲ ኃላፊዎችን ጨምሮ 600 የሚሆኑ ጡረታ የወጡ የደህንነት ባለሥልጣናት ቡድን ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል የጋዛን ጦርነት በአስቸኳይ እንድታቆም ግፊት እንዲያደርጉ የሚጠይቅ ደብዳቤ ፅፈዋል።

የቀድሞ ባለስልጣናቱ በደብዳቤያቸው ሐማስ ከአሁን በኋላ በእስራኤል ላይ ስትራቴጂያዊ ስጋት አይሆንም ሲሉ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

‘‘አብዛኞቹ እስራኤላውያን ያምንዎታል፤ ይህም ጠቅላይ ሚኒስትርን ቤንያሚን ኔታንያሁ እና መንግሥታቸውን ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ የመምራት አቅምዎትን ይጨምራል፤ ጦርነቱን ይቁም፣ ታጋቾችን ይመልሱ፣ ስቃዩን ያቁሙ” ሲሉም በደብዳቤው ጽፈዋል።

ይህ የተማፅኖ ጥያቄያቸው የመጣው ኔታንያሁ ከሐማስ ጋር በተዘዋዋሪ የሚያደርጉት የተኩስ አቁም ድርድር በመቋረጡ በጋዛ የሚደረገውን ወታደራዊ ዘመቻ ለማስፋት ግፊት እያደረጉ መሆኑ በተዘገበበት ወቅት ነው።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review