ኤ ኤም ኤን በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም ተሳትፎን እያደረገ መሆኑን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናገሩ

You are currently viewing ኤ ኤም ኤን በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም ተሳትፎን እያደረገ መሆኑን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናገሩ

AMN – ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም

ኤ ኤም ኤን ታሪክን ከመንገር፣ የዛሬ ልማትን ከማብሰር እና ነገን ከመተንበይ ባሻገር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም ተሳትፎን እያደረገ መሆኑን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናገሩ

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ አመራሮች እና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸዉን አሳርፈዋል፡፡

ትናንትን ሳይዘነጋ ዛሬ ላይ ደማቅ ታሪክን ለመፃፍ እየተጋ ነገን የመተንበይ አቅምን የገነባዉ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ከመረጃ ካዝናዎቹ ከፕሮግራሙም ብፌዎች በተደራጀ ቴክኖሎጂ እና በአማራጭ ቋንቋዎች እና በተለያዩ ሞገዶቹ ሁሉንም አካቶ ለሁሉም በሩን ከፍቶ የአዲስ አበባ ልሳን፣ የሀገር ድል አብሳሪ፣ የትናንት የዛሬ እና የነገ ትዉልድ ማሰናሰያ ሆኖ እየሰራ ነዉ፡፡

ወዲህ ደግሞ ማህበራዊ ሀላፊነትን በተግባር ማረጋገጥ በሀገራዊ የጋራ አጀንዳዎች እና ጉዳዮች ላይ ግንባር ቀደም ሆኖ መገኘት መለያዉ አድርጓል፡፡

በሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ያለፉት አመታት ስኬቶች የህዝብን ተነሳሽነት ማላቅ፤ ግንዛቤን ፈጥሮ ከመሰክ መገኘት ላይም እንዲሁ፡፡

በዚህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ ስራ የማይገደበዉ ኤ ኤም ኤን፤ እነሆ ሰራተኞችን አስተባብሮ ለሀገሩ አሻራን ለማኖር በተግባር ተሰይሟል፡፡

የአዲስ ማዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፉ ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጅ እዉቀት እና የመስራት ጉጉትን ባነገቡ አመራሮች እና ሰራተኞች የአዲስ አበባ ከተማ አንደበት፣ የልማት አብሳሪ፣ የህዝብ እና መንግስት አገናኝ ድልድይ በመሆን ሀላፊነቱን እየተወጣ የሚገኘዉ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይም የነቃ ተሳትፎን ያደርጋል ብለዋል፡፡

በሁለት የቴሌቪዥን ቻናሎች በሬድዮ፣ በጋዜጣ እንድሁም በዲጅታል ሚዲያ አማራጮቹ ፍጥነት፣ ጥራት እና ፈጠራን ያቀናጁ መረጃዎችን ለህዝብ የሚያደርሰዉ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ፤ በአረንጓዴ አሻራ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ላይም የአንድ ጀንበር ስኬቶችን ከሀገሪቱ አራቱም ማዕዘናት ማሳየትን ጨምሮ የማይደበዝዝ ታሪክን ፅፏል ፡፡

ባለፉት አመታት በአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የችግኝ ተከላ ላይ የተቋሙ አመራሮች እና ሰራተኞች የነቃ ተሳትፎን አድርገዋል ያሉት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ፤ ሚዲያዉ በሀገር የሚመዘገቡ ስኬቶችን ከመዘገብ እና ድል አብሳሪ ከመሆን ባሻገር የሀገራዊ ስኬቶች ተቋዳሽ እና የታሪክ አካል እየሆነ ነዉ ብለዋል፡፡

በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተቋሙ እና ሰራተኞች ግንባር ቀደም ሆነዉ ይገኛሉ ያሉት ሀላፊዉ የዛሬዉ የችግኝ ተከላም ሀገራዊ የጋራ ጉዳይን በጋራ ለማሳካት የተደረገ ነዉ ብለዋል፡፡

በቀጣይም የተተከሉ ችግኞች ይፀድቁ ዘንድ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review