በቻይና ዜጂያንግ ግዛት ውስጥ የምትገኘው ሜይሊን መንደር የፀሐይ ኃይል ማመንጫን በመጠቀም የካርበን ልቀት መጠንን መቀነስ ችላለች።
አሸዋማ ሜዳ አካባቢ ያላት የገጠር መንደሯ ሜይሊን፣ ነዋሪዎቿ ከጋዝ እና ከሰል ይልቅ በከፍተኛ ደረጃ የፀሐይ ኃይል ማመንጫን ይጠቀማሉ።
ከሩዝ ማሳዎቻቸው በላይ፣ በመኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ጣሪያ ላይ በብዛት ተገጥመው የሚታዩት የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች፣ የከተማዋን የካርበን ልቀት በዓመት በ268 ሜትሪክ ቶን መቀነስ አስችለዋል።
በተጨማሪም እነዚህን የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች በመጠቀም ከ300 በላይ የሚሆኑ አባወራዎች ኃይል ማግኘት ችለዋል።
መንደሯ በዚህ የካርበን ልቀትን መቀነስ ባስቻለ የነዋሪዎቿ አኗኗር ዘይቤም ለሌሎች አካባቢዎች ሞዴል ትሆናለች ሲል ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።
በሊያት ካሳሁን