አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ አቀረቡ

You are currently viewing አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ አቀረቡ

AMN- ሐምሌ 29/2017 ዓ/ም

በሶማሊያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መለዕክተኛ እና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ፣ የሹመት ደብዳቤያቸውን በዛሬው ዕለት ለሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ ማህሙድ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ማህሙድ፣ የአምባሳደር ሱሌይማን ደደፎን የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ለሶማሊያ መረጋጋት እና ሀገረ መንግስት ግንባታ ለሰጡት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሁለቱ እህትማማች ሀገሮች በርካታ የጋራ እሴት ያላቸው መሆኑ፣ ሰላማቸው እና ልማታቸው በእጅጉ የተያያዘ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ በበኩላቸው፣ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል አመስግነው በሶማሊያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ተግተው እንደሚሰሩ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review