በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኮሚሽኑ ልዑክ ከዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር ተወያይቷል፡፡
በአካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናው የኮሚሽኑ ልዑክ ትላንት ከሰዓት በአካባቢው ከሚገኙ የተለያዩ የዲያስፖራ አደረጃጀቶች እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የስራ አመራሮች ጋር መወያየቱን በኮሚሽኑ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አስተባባሪ አቶ ረታ ጌራ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ ገልጸዋል፡፡
ልዑኩ ትላንት በጠዋቱ መርሀግብር የመጀመሪያ ውይይቱን በሀገሪቱ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አምባሳደር ደሊል ከድር እና ከኤምባሲው ሰራተኞች ጋር ማካሄዱንም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡