6 ተራሮችን ለሚወጡ ተማሪዎች የተዘጋጀ ስኮላርሺፕ

You are currently viewing 6 ተራሮችን ለሚወጡ ተማሪዎች የተዘጋጀ ስኮላርሺፕ

AMN- ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም

በኮሪያ የሰሁል ብሔራዊ ዩኒቨርስቲ ስድስት ተራሮችን ወጥተው በስኬት ለሚያጠናቅቁ ሰዎች የትምህርት ክፍያ ለመሸፈን ዝግጁ ሆኗል።

እስከ አሁን ድረስ 1ሺ 400 ተማሪዎች የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ተመዝግበዋል፡

“ሚሳን ተራራ የመውጣት ስኮላርሺፕ” የተሰኘው መርሀ ግብር 3 ተራሮችን ወጥተው ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች 216 ዶላር እና 6 ተራሮችን ለሚወጡት ደግሞ 540 ዶላር የትምህርት ወጪ የሚሸፍን የስኮላር ሺፕ ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

በፈረንጆቹ 1963 የተጀመረው እና በዓይነቱ ለየት ያለው ስሾላርሺፑ፣ 70 ተማሪዎችን ብቻ ሲያሳትፍ ቆይቷል።

በዘንድሮው 1ሺ 400 ተማሪዎች የተመዘገቡበት በመሆኑ ውድድሩን ከባድ እንደሚደርገው ይጠበቃል።

የዚህ ለየት ያለ ስኮላርሺፕ ዓላማ ሰዎች ፈታኝ ሁኔታዎችን መጋፈጥ እንዲለማመዱ እና ጤናቸውንም መጠበቅ እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ሲል ዩፒአይ ዘግቧል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review