አሜሪካ ከማላዊ እና ከዛምቢያ ለጉብኝት ወይም ለንግድ ቪዛ ለሚፈልጉ ዜጎች15,000 ዶላር ተቀማጭ እንዲከፍሉ ትጠይቃለች ሲል የአሜሪካ መንግስት ማሳወቁን ቢቢሲ ዘግቧል።
ከማላዊ እና ዛምቢያ ውጭ ያሉ ሀገራት ዜጎችም በቅርቡ ተመሳሳይ ተቀማጭ ገንዘብ መክፈል ሊያስፈልጋቸው እንደሚችል ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።
አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ-ወጥ ስደትን ለመግታት የያዙትን አጀንዳ ለማሳካት ፤ በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ተመልክቷል።
እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 በአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት ክፍል በተገኘው መረጃ ፤ 14 በመቶ ያህሉ የማላዊ ጎብኚዎች ቪዛቸው የሚቆይባቸው መሆኑ ታውቋል።
ሄይቲ 31 በመቶ፣ ማይናማር 27 በመቶ እና የመን 20 በመቶ ከፍተኛ የቪዛ መቆየት ያለባቸው ሀገሮች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከ12 ሀገራት የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን ወደ አሜሪካ እንዳይጓዙ ከልክለው በሌሎች ሰባት ሀገሮች ላይ ከፊል እገዳ የጣሉ ሲሆን በመቶዎች ለሚቆጠሩ አለምአቀፍ ተማሪዎች ቪዛ መሰረዙ ተዘግቧል።
በብርሃኑ ወርቅነህ