ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚገናኙ ገለፁ

You are currently viewing ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር እንደሚገናኙ ገለፁ

AMN-ነሀሴ 01/2017 ዓ.ም

ከቀጣዩ ሳምንት አስቀድሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው ጋር በአካል ተገናኝተው እንደሚመክሩ አስታውቀዋል።

የትራምፕ ልዩ መልዕክተኛው ስቲቭ ዊትሆቭ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር በሞስኮ ተገናኝተው ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ነው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፑቲን ሊገያኙ እንደሚችሉ የገለፁት።

ልዩ መልዕክተኛው ከፑቲን ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል ያሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነትም በቀናት ወይም በሳምንታት ውስጥ ለማስቆም ይሰራሉ ብለዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ በሞስኮ የተካሄደውን ውይይት አስመልክቶ ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል ።

ፍላጎታችን ጦርነትን ማስቆምና በዩክሬን አስተማማኝ ሠላም ማምጣት ነው ሲሉም ገልፀዋል።

ሩሲያግ ጭቱን እንድታቆም የሚደረገው ጫና ውጤት እያመጣ መሆኑን ያነሱት ዘሌንስኪ አሁን ላይ ወደ ተኩስ አቁም ስምምነት ለመምጣት ፍላጎት እያሳያች ያለ ይመስላልም ነው ያሉት።

ይሁንና ዝርዝር የተኩስ አቁም ነጥቦች ላይ ሩሲያ እኛንም ሆነ አሜሪካንን እንደማታታልል ሊረጋገጥ የሚገባው መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ ሳምንት ከመግቱ አስቀድሞ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በአካል እንደሚያገኟቸው የገለፁትም ፑቲን ከዘሌንስኪ ጋር በሚኖራቸው ንግግር ላይ እንደሚመሰረት ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጣቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review