አደጋውን ተከትሎም ሀገሪት ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ የሀዘን ቀን አውጃለች።
በሄሊኮፕተር አደጋው የጋና መከላከያ ሚኒስትር ኤድዋርድ ኦማኔ ቦአማህ እና የአካባቢ ጥበቃ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ኢብራሂም ሙርታላ ሙሀመድ እንዲሁም የተጨማሪ አምስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
ሶስት የበረራ አባላትንና አምስት መንገደኞችን ያሳፈረችው Z-9 የተሰኘችው ሄሊኮተር ከመከስከሷ አስቀድሞ ከራዳር እይታ ውጭ ሆና ነበር ተብሏል።
ባለሥልጣናቱ ከጋና ዋና ከተማ አክራ ተነስተው ህገ ወጥ የማዕድን ቁፋሮ በስፋት ወደሚካሄድባት ኦቡአሲ ከተማ ሲበሩ ነው ድንገተኛው የመከስከስ አደጋ ያጋጠማቸው።
የጉዞው ዓላማም በአካባቢው የተንሰራፋውን ህገ ወጥ የማዕድን እንቅስቃሴ ለመካለከል እንደነበር ተገልጿል።
ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማህማ ከሀሙስ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቆይብሔራዊ የሀዘን ቀን ማወጃቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
በተጠቀሱት ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማም ዝቅ ብሎ የሚውለበለብ ሲሆን የአደጋው መንስኤም ተጣርቶ ይገለፃል ተብሏል።