የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገው ቅድመ ውይይት የተሳካ እንደነበር አስታወቀ

You are currently viewing የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገው ቅድመ ውይይት የተሳካ እንደነበር አስታወቀ

AMN – ነሀሴ 2/2017 ዓ.ም

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያየ ባለድርሻ አካላት ጋር ያደረገው ቅድመ ውይይት የተሳካ እንደነበር አስውቋል፡፡

የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ፣ ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል ከጊዚያዊ አስተዳድሩ፣ ከሲቪክ ተቋማት እና ከፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ገልጸው፣ ጊዚያዊ አስተዳድሩ ስለ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያለው ምልከታ አወንታዊ መሆኑን ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል በነበረው ቅድመ ውይይትም በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፖርቲዎች ጋር ስለመወያየቱ ቃል አቀባዩ አክለዋል ።

በቀጣይም የተሳታፊ ልየታ ለማድረግ እቅድ መያዙን የተገለፁ ቃል አቀባዩ፣ የትግራይ ህዝብ በምክክር ሂደቱ ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ በተጨማሪም በውጭ ሀገራት እና በበይነ መረብ ውይይቶችን እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በነገው እለትም በደቡብ አፍሪካ አጀንዳ ማሰባሰብ ስራዎችን የሚያከናውን ሲሆን በቀጣይም በሌሎች ሀገራት አጀንዳዎችን የማሰባሰቡን ስራ እንደሚያከናውን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በወንድምአገኝ አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review