ለሴቶች የሚደረጉ ድጋፎች የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች የመፍታት አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing ለሴቶች የሚደረጉ ድጋፎች የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች የመፍታት አቅማቸው ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 2/2017 ዓ.ም

ለሴቶች የሚደረጉ ድጋፎች የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች የመፍታት አቅማቸው ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ሴቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

“ብራይት ስታር ሪልፍ ኤንድ ዴቭሎፕመንት አሶሴሽን” በጉለሌ ክፍለ ከተማ በምገባ ማዕከል ውስጥ ለነበሩ ሴቶች የራሳቸውን ስራ እንዲፈጥሩ የእንጀራ መጋገሪያ ምጣዶችንና የችብስ መጥበሻ መሳሪያዎችን ድጋፍ አድርጓል፡፡

በተመሳሳይም ለደንብ አስከባሪዎች ለማረፊያ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች እና ለፖሊስ አባላትም ለቢሮ ሥራ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርገዋል፡፡

ለሴቶች የሚደረጉ ድጋፎች የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች መፍታት ነው ያሉት የብራይት ስታር ሪልፍ ኤንድ ዴቭሎፕመንት አሶሴሽን ቦርድ ሰብሳቢ ግዛቸው አይካ (ዶ/ር)፣ አሁን የተደረገውም የማስጀመሪያ ድጋፍ የ90 ቀናት በጎ ፍቃድ አንዱ አካል እንደሆነም አንስተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በምገባ ማዕከል ያሉ ሴቶች ራሳቸውን እንዲችሉ እየሰራ ይገኛል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ፣ የተጀመረው ስራ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሶፍያ ዓለሙ በበኩላቸው፣ ለሴቶች የሚደረጉ ድጋፎች የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ በመሆናቸው፣ ይህ በጎ አድራጎት ተግባር እንደሚያበረታታ ተናግረዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ከፍሎችም ድጋፉ የቀጣይ ስራቸውን ለመለወጥ አጋዥ መሆኑን ጠቁመው፣ ለወደፊትም በርትተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

በመጪው አዲስ ዓመትም “በአዲስ ዓመት አዲስ ጫማ” በሚል መሪ ሀሳብ ለተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግም ብራይት ስታር ገልጿል፡፡

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review