የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሚቀጥለው ሳምንት ሊገናኙ ይችላሉ ሲሉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ ምክትል አምባሳደር ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ነገር ግን ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ በፑቲን እና ዘለንስኪ መካከል ስለታቀደው ስብሰባ እና የት ቦታ እንደሚደረግ አለማወቃቸውን ተናግረዋል።
ፑቲን እና የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ ሰኔ 2021 በጄኔቫ ከተገናኙ በኋላ፣ በሁለቱ ሀገራት መሪዎች መካከል ምንም አይነት ጉባኤ አለመደረጉ ተዘግቧል።
የሩሲያው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል አምባሳደር ዲሚትሪ ፖሊያንስኪ፣ የእስራኤል እና የፍልስጤምን ጦርነት በተመለከተ የጋዛ ሰርጥን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ማንኛውንም የእስራኤል እቅድ ማውገዛቸውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ምንም እንኳን እስራኤል ላይ ዓለም አቀፋዊ ትችቶች እየጨመሩ ቢመጡም፣ እስራኤል ጋዛን ሙሉ በሙሉ በወታደራዊ ቁጥጥር ስር ለማድረግ እያሰበች መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
በብርሃኑ ወርቅነህ