በኬኒያ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

You are currently viewing በኬኒያ በደረሰ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም

በኬኒያ ርዕሰ መዲና አቅራቢያ በሚገኝ ህዝብ በሚበዛበት አካባቢ የህክምና ቡድኖችን ያሳፈረ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

በአምሪፍ የሚተዳደረው እና የህክምና ባለሙያዎችን የሚያጓጉዘው ሴስና የተሰኘው አውሮፕላን ወደ ሶማሌላንድ መዲና ሀርጌሳ በመብረር ላይ ሳለ መከስከሱን ግብረ ሰናይ ድርጅቱ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል።

በአደጋው በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ አራት ሰዎች እና ምድር ላይ የነበሩ 2 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን በአካባቢው ኪያምቡ የተሰኘችው ግዛት ኮሚሽነር ሄነሪ ዋፉላ ተናግረዋል፡፡

አውሮፕላኑ ከዊልሰን አየር ማረፊያ ከተነሳ ከሦስት ደቂቃዎች በኋላ ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ያለው ግንኙነት መቋረጡን የኬኒያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review