ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ጉዳይ ላይ በመጪዉ አርብ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ሊመክሩ ነዉ

You are currently viewing ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ጉዳይ ላይ በመጪዉ አርብ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ሊመክሩ ነዉ

AMN ነሃሴ 3/2017 ዓ.ም

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን የተኩስ አቁም ስምምነት ጉዳይ ላይ ከሩሲያዉ አቻቸዉ ቭላድሚር ፑቲን ጋር በአላስካ እንደሚገናኙ ተገልጿል።

ሁለቱ መሪዎች በአካል ተገናኝተዉ እንደሚመክሩ በተደጋጋሚ ቢገለጽም ቀነ ገደባቸዉ ሳይሳካ ቀርቷል።

እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ ዩክሬን በስምምነቱ ማድረግ ያለባትን ዶናልድ ትራምፕ ከወዲሁ ፍንጭ ሰጥተዋል።

ይህም ሁለቱ ሃገራት አንዳንድ ግዛቶችን መለዋወጥ የሚያስችላቸዉን ሃሳብ በስምምነቱ ዉስጥ ሊያካትቱ ይገባል ሲሉ መናገራቸዉ ነዉ።

አዉሮፖ የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በኦላስካ ለመገናኘት በያዙት ቀጠሮ ላይ እንድትገኝ አልተጋበዘችም። ኪየቭም ቀጠሮዉንና እየተሰነዘሩ ያሉትን ሃሳቦች አአስመልክቶ እስካሁን ድረስ ያለችዉ ነገር የለም።

ይሁን እንጂ ዩክሬን ግዛቷን ለሩሲያ የምታስረክብበትን ስምምነት ዋይት ሀውስ እያቀረበች መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል።

ቭላድሚር ፑቲን ከ2019 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከትራምፕ ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ወደ አሜሪካ ለመሄድ ማቀዳቸዉን ክሬምሊን አረጋግጣለች።

ሞስኮ ከ2022 ጀምሮ ባካሄደችው አጠቃላይ ወረራ ወሳኝ ለውጥ ማምጣት ቢሳናትም 20 ከመቶ የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት ይዛለች።

በሌላ በኩል የዩክሬን ጥቃቶች የሩስያ ሀይሎችን ወደ ኋላ ሊመልስ አልቻለም።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review