በሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ ታገደ

You are currently viewing በሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ ታገደ

AMN ነሐሴ 2/2017

በሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሰማሩ 138 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ መታገዱን የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ገለጸ፡፡

አገልግሎቱ ለኤኤምኤን በላከው መግለጫ ሕጋዊና መደበኛ የባንክ ስርዓትን ወደ ጎን በመተው በህገ-ወጥ እና ትይዩ ገበያ የውጭ ምንዛሪ ወንጀል ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ ተደርጓል ብሏል፡፡

የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት በሕጋዊና መደበኛ የባንክ ሥርዓት በኩል እንዲከናወን በግልጽ የተቀመጠ መሆኑን ያወሳው መግለጫው፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የምንዛሪ አገልግሎት ላይ የተሰማሩት ላይ ጠንካራ የሕግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ ላይ ተሰማርቶ መገኘት የንብረት መወረስን ጨምሮ በከፍተኛ ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ መደበኛ የባንክ ስርዓትን እንዲጠቀም በመንግስት በኩል ማሳሳቢያ ሲሰጥ ቆይቷል ብሏል።

ሆኖም ግን አንዳንድ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ወንጀልን እንደ መደበኛ የንግድ ስራ በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በመሆናቸው ክትትል ሲደረግባቸው ቆይቷል ሲል ገልጿል።

በዚሁ መሠረት ክትትል ተርጎ የተደረሰባቸው እና በህገ-ወጥ የውጭ ምንዛሪ ላይ የተሰማሩ 138 ዋነኛ ተጠርጣሪዎች የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲታገድ መደረጉን ነው አገልግሎቱ በመግለጫው ያስታወቀው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review