እስራኤል ጋዛን ለመቆጣጠር ካጸደቀችዉ እቅድ ጋር ተያይዞ የደረሰባትን አለም አቀፍ ዉግዘት ዉድቅ በማድረግ በእቅዷ እንደምትገፋ ማስታወቋን ቢቢሲ ዘግቧል።
እስራኤል ያወጣችዉ እቅድ ሃማስን ጦር የማስፈታት፣ ታጋቾቿን ማስመለስን እና የሃማስንም ሆነ የፍልስጤምን ባለስልጣናት ያላካተተ አዲስ አስተዳደርን በከተማዋ መመስረትን ያጠቃልላል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ እና ካናዳ የእስራኤልን አዲስ እቅድ በከፍተኛ ደረጃ ያወገዙ ሲሆን፤ ጀርመንም እቅዱን ተከትሎ ወደ እስራኤል ታደርግ የነበረውን ወታደራዊ ድጋፍ አቋርጣለች።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት እና የሃገራቱ መሪዎች የእስራኤል እቅድ ተጨማሪ ግጭት የጅምላ መፈናቀል እና ሰብአዊ ቀውስን ያባብሳል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
እስራኤል ከውስጥም ቢሆን፤ በዋነኛነት ከወታደራዊ ባለስልጣናት እና ከቀሪ የታጋች ቤተሰቦች ተቃውሞዎች እየተነሱባት ነው።
ሃማስም እስራኤልን በጦር ወንጀልነት የፈረጀ ሲሆን አፀፋውን እንደሚመልስ አስታውቋል።
በሊያት ካሳሁን