የማንችስተር ዩናይትዱ አዲሱ ፈራሚ ክለቡን በመቀላቀሉ ደስተኛ እንደሆነ ተናግሯል ።
የ22 ዓመቱ አጥቂ ” የማንችስተር ዩናይትድ ታሪክ የገዘፈ እንደሆነ ይታወቃል ፤ እኔን የገዛኝ የወደፊት እቅዱ ነው ።” ሲል ተናግሯል።
ያለኝን ብቃት ለማሳደግ እና ምኞቴን ለማሳካት ዩናይትድ ትክክለኛው ቦታ ነው ያለው ሼሽኮ መለያውን አጥልቆ ወደ ሜዳ እስከሚገባ መቸኮሉን ገልጿል ።
ፉትቦል ዳይሬክተሩ ጄሰን ዊልኮክስ “ሼሽኮ ዓለም ላይ ካሉ ድንቅ ወጣት ባለተሰጥኦዎች አንዱ ነው ። እርሱን በጥብቅ ስንከታተለው ነበር ፤ በክትትላችን በዩናይትድ ሊሳካለት የሚያስችል አቅም እንዳለው አይተናል ። ” ሲሉ ተናግረዋል ።
ቤንጃሚን ሼሽኮ በጀርመኑ ክለብ ላይብዚግ የሁለት ዓመት ቆይታው 39 ግቦችን አስቆጥሯል ።
የግብ መጠኑ በአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ዕድሜያቸው ከ23 ዓመት በታች ከሆኑ ተጫዋቾች በርካታ ግብ ያስቆጠረ ቀዳሚው ተጫዋች ያደርገዋል ።
በሸዋንግዛው ግርማ