ሰላምን ለማጽናት የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ

You are currently viewing ሰላምን ለማጽናት የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ

AMN ነሐሴ 3/2017

በመላ ሀገሪቱ ሰላምን ለማጽናት የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገለጹ።

በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት የሁሉም ክልሎች እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ አመራሮች ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።

በዚሁ ወቅት “ሰላምን ማጽናት ለሀገራዊ ማንሠራራት” በሚል የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ላይ ትገኛለች ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸው ሰላምን ከማጽናት አኳያ አመርቂ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

በመላ ሀገሪቱ ሰላምን ለማጽናት የሰላምና ፀጥታ ዘርፍ አመራሮች ሚናቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልጸዋል።

በማህበረሰቡ ዘንድ ያለውን ዘመን ተሻጋሪ የአብሮነት እሴት ይበልጥ ማጎልበት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

ዘላቂ ሰላምን በማፅናት የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ ባህላዊ የግጭት አፈታት ጥበቦችን በአግባቡ መጠቀምና ችግሮችን በሰላም መፍታት እንደሚገባ መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በየአካባቢው ያሉ ሀገር በቀል የሰላም ማፅኛ ጥበቦችንና የተሻለች ሀገርን ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል ነው ያሉት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review