የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሰራተኞች ማህበር አባላት ጋር በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሰራተኞች ማህበር አባላት ጋር በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ

AMN ነሐሴ 3/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሰራተኞች ማህበር አባላት ጋር በመሆን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

የችግኝ ተከላው በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ቤላ 18 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው የተከናወነው።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የሰራተኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ኑሁ ቺያም እንዳሉት፤ የአየር ንብረት ለውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።

በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚመጡ ችግሮችን በዘላቂነት ለመከላከል ችግኞችን መትከል ሁነኛ መንገድ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያመጣቸው ውጤቶች በአርዓያነት የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይመር ከበደ በበኩላቸው፤ የዛሬው ችግኝ ተከላ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ የሰጠችውን ትኩረት በተጨባጭ ለማሳየት ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ይህም የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባት በኩል ሚናው የላቀ መሆኑን ማስረዳታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ በአህጉር ደረጃ አጀንዳ እንዲሆን የተጀመረው ጥረት ግቡን እንዲመታ በማድረግ ረገድ የዛሬው መርኃ ግብር ከፍ ያለ አበርክቶ እንደሚኖረውም አብራርተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review