አርሰናል ከአትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ያደረገውን የኤምሬትስ ካፕ ጨዋታ አሸንፏል።
የሰሜን ለንደኑ ክለብ 3ለ0 ባሸነፈበት ጨዋታ አዲስ ፈራሚው አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ ለክለቡ የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሯል ።
ቡካዮ ሳካ እና ካይ ሃቨርትዝ ሌሎቹን ግቦች በስማቸው አስመዝግበዋል ።
መድፈኞቹ በስፖንሰራቸው ኤምሬትስ አማካኝነት ክለቦችን እየጋበዙ በየዓመቱ በሜዳቸው የሚያዘጋጁት ጨዋታ ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ ተከናውኗል።
ኤምሬትስ ካፕን አርሰናል ዘጠኝ ጊዜ በማሸነፍ የበላይ ነው ።
አርሰናል የፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን ቀጣይ ሳምንት እሁድ ወደ ኦልድትራፎርድ በማቅናት ያከናውናል ።
በሸዋንግዛው ግርማ