በኪሎ 30 ሺህ 204 ዶላር የተሸጠው ቡና

You are currently viewing በኪሎ 30 ሺህ 204 ዶላር የተሸጠው ቡና

AMN – ነሐሴ 3/2017 ዓ.ም

የፓናማ ምርጥ የሚል ስያሜ በተሰጠዉ የ2025 የአለም አቀፍ የፓናማ የቡና ጨረታ ላይ ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው የጌሻ ቡና በኪሎ 30 ሺህ 204 ዶላር በመሸጥ አዲስ የአለም ክብረ ወሰን ሰብሯል።

የፓናማ ልዩ ቡና ማህበር የሚያዘጋጀው ጨረታ በፈረንጆቹ 1990 የተጀመረ ሲሆን በ2004 አለም አቀፍ እውቅናን በማግኘት በአሁኑ ሰዓት አለም አቀፍ ገዢዎችን በበይነ መረብ በማሳተፍ የሚካሄድ የፓናማ የቡና ጨረታ ሆኗል፡፡

ፓናማ የቡና ምርቶቿን ለማስተዋወቅ በምትጠቀምበት በዚህ ጨረታ ላይ በዚህ ዓመት ከቻይና፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ዱባይ፣ አሜሪካ፣ ካናዳ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት የተውጣጡ ተጫራጮች ተሳትፈዋል።

በጨረታውም ከሃሲዬንዳ ላ ኤስሜራልዳ እርሻ የተገኘው ‘የታጠበ ጌሻ’ የተባለው የቡና ዝርያ ለጨረታ ከቀረቡ 50 የቡና ዝርያዎች በኪሎ 30 ሺህ 204 ዶላር ለዱባይ ገዢ በመሸጥ ክብረ ወሰንን ይዟል።

ጌሻ ቡና ምንጩ ኢትዮጵያ የሆነው የአረቢካ ቡና ዝርያ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ዩ ፒ አይ ነው።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review