ኮሚሽኑ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ተረከበ

You are currently viewing ኮሚሽኑ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ተረከበ

AMN ነሀሴ 3/2017 ዓ.ም

ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናው የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ልዑክ ቡድን በሀገሪቱ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ያሰባሰበበትን መድረክ ዛሬ በሀገሪቱ መዲና ፕሪቶሪያ አካሂዷል።

መድረኩን ለማካሄድ ከተለያዩ አካላት ጋር ሲወያይ የቆየው ቡድኑ ዛሬ የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረኩን አከናውኖ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች ተረክቧል።

የኮሚሽኑ ልዑክ ባለፈው ሳምንት ሀምሌ 28/2017 ዓ.ም በአካባቢው ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ ለማሰባሰብ ወደ ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ማቅናቱ አይዘነጋም።

ኮሚሽኑ በቀጣይ በሰሜን አሜሪካ፣ በካናዳ፣ በእንግሊዝ፣ በሲውዲንና በዱባይ ተመሳሳይ መድረኮችን በማካሄድ አጀንዳዎችን የሚሰበስብ መሆኑን ኮሚሽኑ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review