ክሪስታል ፓላስ ሊቨርፑልን በመለያ ምት በማሸነፍ የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ባለድል ሆኗል ።
በጨዋታው የ22 ዓመቱ ፈረንሳዊ አጥቂ ሁጎ ኢኪቲኬ በግሩም አጨራረስ ያስቆጠረው ግብ ሊቨርፑልን መሪ አድርጓል ።
የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊው ፓላስ ዦን ፍሊፕ ማቴታ ባስቆጠረው የፍፁም ቅጣት ምት አቻ መሆን ችሏል ።
ሊቨርፑል ብዙም ሳይቆዩ በጀርሚ ፍሪምፖንግ ግብ መሪነታቸውን መልሰዋል ።
በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫ የወሰዱት ፓላሶች ግን ኢስማኤላ ሳር ባስቆጠረው ግብ በድጋሚ አቻ ሆነዋል ።
መደበኛው 90 ደቂቃ 2ለ2 ተጠናቆ በተሰጠ መለያ ምት ክሪስታል ፓላስ 3ለ2 አሸንፎ ባለድል ሆኗል ።
በመኪና አደጋ ሕይወቱን ያጣው ዲያጎ ጆታ በታሰበበት ጨዋታ ፓላስ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ባለቤት ሆኗል ።
በሸዋንግዛው ግርማ