የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ነሐሴ 4/2017 ዓ.ም

የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ለመጠቀም እየተሰራ እንደሆነና በሀገር ደረጃ ያሉ ባህላዊ የችግር አፈታት ስርዓቶችን ለሀገር ግንባታ የማዋል ስራዎችም እየተሰሩ መሆናቸውን የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገለጹ።

በሰላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የሰላምና ጸጥታ ዘርፍ አመራሮች በአዳማ ያካሄዱት የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

ምክክሩ “ሰላማችንን ማጽናት ለኢትዮጵያ ማንሠራራት ” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የተካሄደው።

በውይይቱ ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ ሰላምን እና ልማትን በማቀናጀት መተግበር ይገባል ብለዋል።

ለሀገር ግንባታ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቁመው፣ የሀገርን ከፍታ ለማረጋገጥ በሁሉም ዘርፎች ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ለመጠቀም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ በሀገር ደረጃ ያሉ ባህላዊ የችግር አፈታት ስርዓቶችን ለሀገር ግንባታ የመጠቀም ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ለመጪው ትውልድ ሁለንተናዊ ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገር ለማስረከብ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ሰላምን ዘላቂ ማድረግ የሁሉም ሚና መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።

ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ስኬታማነት ሰላምን ማጽናት የሁሉም ኃላፊነት መሆን እንዳለበትም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review