የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር እቅድ ተቸ

You are currently viewing የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ጋዛን የመቆጣጠር እቅድ ተቸ

AMN – ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም

የተባበሩት መንግሥታት አምባሳደሮች እስራኤል የጋዛ ከተማን ለመቆጣጠር ያያዘችውን ዕቅድ ተችተዋል።

ትችቱን ተከትሎ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦርነቱን ለማስቆም የተሻለው መንገድ ይህ ነው ብለዋል።

ኔታንያሁ ‘ውሸቱን ለማጋለጥ’ ብለው በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫቸው፣ የታቀደው ዕቅድ በአመዛኙ በፍጥነት የሚከናወን እንደሆነና ጋዛን ከሃማስ ለነፃ ለማውጣት ያቀደ መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም እስራኤል ጋዛዊያንን እያስራበች ነው የሚለወን ትችት አስተባብለዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ወቅት እስራኤል ከበርካታ የምክር ቤቱ አባል ሃገራት እቅዷ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ ህግን ይጥሳል በሚል ጠንካራ ትችት ገጥሟታል።

አሜሪካ በተቃራኒው ለጦርነቱ መቀጠል ሃማስን ተጠያቂ በማድረግ ለእስራኤል ተከላክላለች።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review