የምስራቅ ዕዝ የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማጽናት ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ ገለጹ

You are currently viewing የምስራቅ ዕዝ የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማጽናት ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ ገለጹ

AMN ነሐሴ 5/2017

የምስራቅ ዕዝ የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማጽናት ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ የዕዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ ተናገሩ።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ 48ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በሐረር ኢማም አህመድ ስታድየም በስፖርት ፌስቲቫል መከበር ጀመሯል።

በበዓሉ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት ሌተናል ጀነራል መሐመድ ተሰማ ምሥራቅ ዕዝ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለህዝቦች ደህንነት መከበር ከፍተኛ ተጋድሎ ካደረጉ ዕዞች መካከል አንዱ ነው ብለዋል።

ሰራዊቱ ኢትዮጵያዊነትን መላበሱ፣ አኩሪ ባህሪና እሴቶችን መጠበቁና ህዝቡ ለሰራዊቱ የሰጠው ክብር ለውጤታማነቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል።

ዕዙ ከሌሎች ዕዞች ጋር በመሆን ህዝባዊ ባህሪያትና እሴቶችን በመጠበቅ ኢትዮጵያን ከውስጥም ሆነ ከውጪ ጥቃቶች በመከላከል የተሰጠውን ተልኮ አጠናክሮ ቀጥሏል።

በቀጣይም ዕዙ የሀገር ሉዓላዊነትን የማስጠበቅና ሰላምን የማጽናት ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

የምሥረታ በዓሉን “ህገ መንግስታዊ ተልዕኳችንን በድል እየተወጣን የሀገራችንን ሰላም እናፀናለን” በሚል መሪ ሃሳብ ለ30 ቀናት ይከበራል ያሉት ደግሞ የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ፀጋዬ ናቸው።

በዓሉም በስፖርታዊ ፌስቲቫል፣ በወታደራዊ ልምምድና ትርዒቶች፣ በፓናል ውይይት፣ በመጽሐፍ ምረቃና በሌሎች ፕሮግራሞች ይከበራል ብለዋል።

እንዲሁም የዕዙን የግዳጅ አፈፃፀም የሚያሳዩ ዘጋቢ ፊልምና የፎቶ ግራፍ ዐውደ ርዕይ ለእይታ እንደሚቀርብም ተናግረዋል።

ዕዙ ከወታደራዊ ግዳጁ ጎን ለጎን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በችግኝ ተከላና እንክብካቤ ስራዎችን ከህዝቡ ጋር ማከናወኑን መግለጻቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በመርሃ ግብሩ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር፣ በብልጽግና ፓርቲ የሐረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ጌቱ ወዬሳ፣ ጀነራል መኮንኖችና የሰራዊቱ፣ የፌዴራልና የክልሉ የፖሊስ አባላትና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review