የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን በጠንካራ መዋቅር የማደራጀት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ገለፁ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽንን በጠንካራ መዋቅር የማደራጀት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ገለፁ

AMN ነሃሴ 05/2017

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ ሰልጣኝ ሰራተኞች አቀባበል በሚሊኒየም አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት የጉምሩክ ኮሚሽን ጠንካራ ተቋም ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።

ሥነ-ምግባር የተላበሱ እና ትጉ የሰው ሀይል ማፍራት፣ ዘመኑን የዋጁ አሰራሮችና ደንቦችን ማዘጋጀት እና ተቋሙን በቴክኖሎጂ የማደራጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኮሚሽኑን በሰው ኃይል ይበልጥ ለማደራጀት ከመላው ሀገሪቱ የተወጣጡ ከሶስት ሺህ በላይ አዲስ ሰራተኞችን መቅጠሩን ተናግረዋል።

አዲስ ባለሙያዎቹ ሥልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ሀገር ለምትሰጣቸው ተልዕኮ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ነው ማሳሰባቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

ኮሚሽኑን በጠንካራ መዋቅር የማደራጀት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review