ማንችስተር ሲቲ ጃክ ግሪሊሽን ለኤቨርተን በውሰት ለመስጠት ተስማምቷል ።
የ30 ዓመቱ እንግሊዛዊ በፔፕ ጋርዲዮላ ተመራጭ አለመሆኑን ተከትሎ ክለቡን ለመልቀቅ ተቃርቧል ።
ለክለቡ ክብረ ወሰን የሆነው 100 ሚሊየን ፓውንድ ወጥቶበት ከአስቶንቪላ ሲቲን የተቀላቀለው ግሪሊሽ በኤቨርተን ውሉን ቋሚ የማድረግ አማራጭም አለው ።
በቀጣይ 24 ሰዓትም ዝውውሩን እንደሚያጠናቅቅ ቢቢሲ ስፖርት ዘግቧል ።
ግሪሊሽ በማንችስተር ሲቲ የአራት ዓመት ቆይታው ሰባት ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል።
በሸዋንግዛው ግርማ