የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ሕገ ወጥ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን መቆጣጠር በሚቻልበት ሁኔታ
መክረዋል።
ሁለቱ ሃገራት በገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በሚደረገው ቁጥጥር ያላቸውን ትብብር ለማጠናከርና የገንዘብ ዝውውሩ በመደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ መከናወኑን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተነጋግረዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ከባንኩ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።