አሜሪካ እና ቻይና የታሪፍ ጭማሪ ለማስቀረት የንግድ ስምምነት ቀነ ገደብ አራዘሙ

You are currently viewing አሜሪካ እና ቻይና የታሪፍ ጭማሪ ለማስቀረት የንግድ ስምምነት ቀነ ገደብ አራዘሙ

AMN – ነሃሴ 6/2017

አሜሪካና ቻይና የታሪፍ ጭማሪዉ ተግባራዊ ከመሆኑ ከሰአታት በፊት የንግድ ውላቸውን ለተጨማሪ 90 ቀናት ማራዘማቸዉ ተዘግቧል።

ሁለቱ የአለማችን ግዙፍ የኢኮኖሚ ባለቤቶች አሜሪካና ቻይና በታሪፍ ጭማሪዉ የንግድ ስምምነት ዙሪያ ባለፈው ወር ያካሄዱትን ዉይይት ገንቢ በማለት ጠርተውታል።

የቻይናው ከፍተኛ ተደራዳሪ በዉይይቱ ወቅቱ እንደተናገሩት ሁለቱ ሀገራት የንግድ ስምምነቱን ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕም ባለፈዉ ሰኞ የታሪፍ ስምምነቱን ለማራዘም ለስራ አስፈፃሚያቸዉ ትዕዛዝ መፈረማቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል።

በንግድ ስምምነቱ መሠረት ዋሽንግተን በቻይና ምርቶች ላይ 145 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ለመጣል ተጨማሪ ቀናቶችን ታዘገያለች።

በተመሳሳይ መልኩ ቤጂንግ በአሜሪካ ሸቀጦች ላይ የጣለቸዉን 125 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ ባለበት እንዲቆይ ታደርጋለች።

በቀደመዉ ስምምነት መሰረት አሜሪካ ከቻይና ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች ላይ 30 በመቶ ታሪፍ ስትጥል ቻይና በበኩሏ በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ10 በመቶ ቀረጥ መጣሏ ይታወሳል።

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review