በበጀት ዓመቱ ለከተማዋ ነዋሪዎች የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች፣ ፍተሃዊ፣ ተደራሽ እና የተገልጋዩን እርካታ የጨመሩ መሆናቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት፣ በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማትን የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ እቅድ እና የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ወይይት አካሂዷል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት ብቻ ከ3.1 ሚሊየን በላይ ዜጎችን የፋይዳ መታወቂያ እንዲመዘገቡ መደረጉን ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ከተማዋን ውብ እና ፅዱ ማድረግ መቻሉን የገለፁት ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም ተግባር 12 ከመቶ መድረሱን ተናግረዋል፡፡
533 የእሳት ተጋላጭ ቦታዎች በመለየት መፍተሄ እንዲያገኙ መደረጉን የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ፣ በበጀት ዓመቱ በተከናወኑ ተገባራት የ12.7 ቢሊየን ብር ንብረት ከእሳት አደጋ ማዳን መቻሉንም ገልፀዋል፡፡
ጨለማ የነበሩ አካባቢዎችን ወደ ብረሃን በመቀየር እና የማይሰሩ የመንገድ ላይ መብራት እንዲሰሩ በማድረግ የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ማሳለጡ ተመላክቷል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ