ኬፕ ቨርዴ በድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ምክንያት አስቸኳይ ጊዜ አወጀች

You are currently viewing ኬፕ ቨርዴ በድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ምክንያት አስቸኳይ ጊዜ አወጀች

AMN- ነሐሴ 07/2017 ዓ.ም

በኬፕ ቨርዴ በተከሰተ ከባድ የጎርፍ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 1ሺህ 500 ሰዎች ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፡፡

በሀገሪቱ ሳኦ ቪሴንት እና ሳንታ አንታኦ በተባሉ ደሴታማ አካባቢዎች የተከሰተው የጎርፍ አደጋ አውዳሚ ነበር ሲሉ የኬፕ ቨርዴ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኦላቮ ኮሬያ ገልፀዋል፡፡

የትሮፒካል አውሎንፋስ የፈጠረው ጫና ያስከተለው ዝናብ የጉዳት መጠኑን ከፍ እንዲል አድርጓልም ተብሏል፡፡

የአደጋ መከላከል ሰራተኞች እስካሁን በህይወት ያልተገኙ ሰዎችን ፍለጋ የቀጠሉ ሲሆን መንገዶች ፣መኖሪያዎች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል፡፡

የሀገሪቱ ሚትዎሮሎጂ ኢንቲትዩት አደጋው ያልተለመደ እና ባለፉት 30 አመታት ከተከሰተው አማካይ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍ ያለ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለተጎጂዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ በሀገር ውስጥ እና በውጭ መጀመሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review