ኤጀንሲዎች የከተማዋን ደረጃ የሚመጥን የጥበቃ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቁመና ላይ መገኘት እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኤጀንሲዎች ሰላም የማጽናት ሚናቸው ከግብ እንዲደርስ ከግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች የሥራ ኃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሄዷል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ኤጀንሲዎቹ የከተማዋን ደረጃ የሚመጥን የጥበቃ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቁመና ሊያጎለብቱ ይገባል ብለዋል፡፡
የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች የሚቀጠሩ የጥበቃ ሰራተኞች ለጥበቃ ብቁ የሚያደርግ መስፈርትን ማሟላት ላይ ትኩረት ማደረግ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡
የግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች የሚቀጠሩ የጥበቃ ሰራተኞች የተቋማትን ደህንነት ከመጠበቅ በሻገር ወንጀልን በመከላከል እና ሰላምን በማፅናት ሂደት ደርሻችንን እንደሚወጡም ለኤ ኤም ኤን ገልፀዋል፡፡
በዳንኤል መላኩ