ፓሪሰን ዠርማ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነ

You are currently viewing ፓሪሰን ዠርማ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነ

AMN – ነሃሴ 08/2017 ዓ.ም

ቶተንሃም ሆትስፐርስ እና ፓሪሰን ዠርማ ያገናኘው 50ኛው የአውሮፓ ሱፐር ካፕ በፈረንሳዩ ክለብ የበላይነት ተጠናቋል።

የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊው ፓሪሰን ዠርማ ጨዋታውን በመለያ ምት ማሸነፍ ችሏል።

መደበኛው 90 ደቂቃ 2ለ2 ሲጠናቀቅ ተከላካዮቹ ሚኪ ቫን ደቬን እና ክሪስቲያን ሮሜሮ የሰሜን ለንደኑን ክለብ ግቦች ከመረብ አሳርፈው እስከ 85ኛው ደቂቃ 2ለ0 መምራት ችለው ነበር ።

በአብዛኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተዳክሞ የታየው ፒ ኤስ ጂ ተቀይረው በገቡት ሊ ካንግ ሊ እና ጎንካሎ ራሞስ ባስቆጠሯቸው ግቦች አቻ ሆኗል ።

የሊውስ ኤነሪኬ ስብስብ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለምን የሦስትዮሽ ድል ባለቤት እንደሆነ በጨዋታው የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ አሳይቷል ።

ፒ ኤስ ጂ በመለያ ምት 4ለ3 በማሸነፍም በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የአውሮፓ ሱፐር ካፕን አንስተዋል ።

የአውሮፓ ሱፐር ካፕን ያሸነፈ የመጀመሪያው የፈረንሳይ ክለብም ሆኗል ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review