ፑቲን የሰላም ድርድሩን የሚያደናቅፉ ከሆነ ከባድ መዘዝ ያስከትላል ሲሉ ትራምፕ አስጠነቀቁ

You are currently viewing ፑቲን የሰላም ድርድሩን የሚያደናቅፉ ከሆነ ከባድ መዘዝ ያስከትላል ሲሉ ትራምፕ አስጠነቀቁ

AMN- ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም

ፕሬዚዳንት ፑቲን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም የማይስማሙ ከሆነ ከባድ መዘዝ እንደሚያስከትል ዶናልድ ትራምፕ አስጠንቅቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ መዘዙ ምን ሊሆን እንደሚችል በግልጽ ባያስቀምጡም፣ ከፑቲን ጋር በአላስካ የሚያደርጉት ስብሰባ ፍሬያማ ካልሆነ ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ ውጤታማ የሚሆን ከሆነ የዩኩሬኑን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪን ያካተተ ሁለተኛ ስብሰባ በፍጥነት እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ስብሰባ በጥሩ ሁኔታ የሚሄድ ከሆነ፣ ሁለተኛውን ዙር ስብሰባ በፍጥነት እናካሂዳለን ሲሉ ነው ትራምፕ ለጋዜጠኞች የተናገሩት፡፡

በነገው ዕለት በአላስካ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር የሚገናኙት ትራምፕ፣ ሁለተኛውን ስብሰባ ግን መች ለማካሄድ እንዳሰቡ ጊዜውን በግልፅ አላስቀመጡም፡፡

መሪዎቹ የእኔን መገኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከፑቲን እና ዜለንስኪ ጋር ሁለተኛውን ስብሰባ በአስቸኳይ ማድረግ ነው የምፈልገው ሰሉ ነው የገለጹት፡፡

ዶናልድ ትራምፕ አክለውም፣ ፕሬዚዳንት ፑቲን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም የማይስማሙ ከሆነ ከባድ መዘዝ ያስከትላል በማለት አስጠንቅቀዋል፡፡

ትራምፕ ከአውሮፓ መሪዎች እና ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ጋር በስልክ ስኬታማ ውይይት እንዳደረጉ መግለፃቸውንም አር ቲ ኢ ዘግቧል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review