ከሽሮ ሜዳ እስከ ኪዳነ ምህረት ያለው የመንገድ ዳር መብራት የነዋሪዎችን ቅሬታ የፈታ መሆኑን ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ

You are currently viewing ከሽሮ ሜዳ እስከ ኪዳነ ምህረት ያለው የመንገድ ዳር መብራት የነዋሪዎችን ቅሬታ የፈታ መሆኑን ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ

AMN- ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም

ከሽሮ ሜዳ እስከ ኪዳነ ምህረት ያለው የመንገድ ዳር መብራት የነዋሪዎችን የረጅም ጊዜ ቅሬታ የፈታ እና የመልካም አሰተዳድር ጥያቄዎችምን የመለሰ ነው ሲሉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ተናገሩ፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ከሽሮ ሜዳ እስከ ኪዳነ ምህረት ያለው የመንገድ ዳር መብራት ያለበትን ደረጃ ከተለያዩ አመራሮች ጋር በምሽት ጎብኝተዋል፡፡

ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ከሽሮ ሜዳ እስከ ኪዳነ ምህረት ያለው የመንገድ ዳር መብራት የነዋሪዎችን የረጅም ጊዜ ቅሬታ የፈታ እና የመልካም አሰተዳድር ጥያቄዎችምን የመለሰ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የሚሰሩት መሰረተ ልማቶች ለማሀበረሰቡ ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሰጡ ስለመሆናችውም ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን በአጭር ጊዜ የተቋቋቀመ ቢሆንም፣ ኃላፊነቱን በአገባቡ እየተወጣ ነው ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ፣ ማህበረሰቡም የተሰሩ መሰረተ ልማቶችን በመጠበቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም አካባቢው የተለያዩ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት እና በምሽት መንቀሳቀስ የሚያዳግት እንደነበር በማስታወስ አሁን የተሰራው የመንገድ መብራት የረጅም ጊዜ ጥያቄያችንን የፈታ ነው ብለዋል።

የመንገድ መብራቶቹ መሰራታችው ከተለያዩ ስጋቶች እንደታደጋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰብስብ ሁሴን፣ ባለስለጣኑ የነዋሪዎች ጥያቄዎች ናቸው የተባሉትን ምላሽ ለመስጠት በጥናት የተደገፈ ስራ መሰራቱን በመጥቀስ፣ የመንገድ ዳር መብራቶቹ በአጭር ጊዜ የተከናወኑ ስለመሆናቸው ተናገረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሠረተ ልማት እና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግዛቸው አይካ (ዶ/ር) የመንገድ ዳር መብራቶቹ በህብረተሰቡ ዘንድ ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል የመንገድ ዳር መብራቶች እንደሚጠቀሱ አስታውሰዋል።

ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችም አካባቢው የተለያዩ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት እና በምሽት መንቀሳቀስ የሚያዳግት እንደነበር በማስታወስ አሁን የተሰራው የመንገድ መብራት የረጅም ጊዜ ጥያቄያችንን የፈታ ነው ብለዋል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review