የዑለማ ምርጫ በነገው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አስታወቀ

You are currently viewing የዑለማ ምርጫ በነገው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አስታወቀ

AMN – ነሐሴ 8/2017 ዓ.ም

ሕዝበ ሙስሊሙ ነገ አርብ፣ ነሃሴ 9 ቀን 2017 ዓ.ም የዑለማ ምርጫ እንደሚያካሂድ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ አብዱልአዚዝ ኢብራሂም (ዶ/ር)፣ የምርጫውን ሂደት በተመለከተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የዑለማ ምርጫውን ስኬታማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ተናግረዋል።

አካታች፣ አሳታፊ፣ ፍትሃዊ እና የሕዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት ያስጠበቀ ምርጫ ለማድረግም ሰፊ ሥራ መሰራቱን ገልፀዋል።

ሂደቱ በክላስተር ተከፋፍሎ የተመራ መሆኑን ያነሱት ሰብሳቢው፣ በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ መስጂዶች ምዝገባ መከናወኑን እና በተለዩት ዘርፎች ላይ ነገ ምርጫው እንደሚካሄድ አመላክተዋል።

ለምርጫው 13 ሚሊየን 151 ሺህ በላይ መራጮች መመዝገባቸው ተገልጿል።

ምርጫው ከነገ ጀምሮ እስከ እሁድ እንደሚከናወን ተመላክቷል።

በትግራይ ክልል አመቺ ሁኔታ ባለመፈጠሩ የምርጫ አስፈፃሚ ቦርዱ በጠየቀው መሰረት ምርጫው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰብሳቢው ተናግረዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review