የ63 ኪሎ ሜትር ውድድር ድል ያደረገቸው ሜክሲኮአዊቷ ሪቫስ

You are currently viewing የ63 ኪሎ ሜትር ውድድር ድል ያደረገቸው ሜክሲኮአዊቷ ሪቫስ

AMN-ነሀሴ 09/2017

አሰልጣኝ እና የስፖርት ትጥቅ የሌላት ሜክሲኮአዊቷ ካንዴላሪያ ሪቫስ ራሞስ በአካባቢው ማህበረሰብ የተለመደውን አለባበስ ለብሳ ነው ውድድሩን የተቀላቀለቸው።

ሜክሲኮአዊቷ ሪቫስ 7 ሰዓት ከ34 ደቂቃ በሆነ ሰዓት ነው ርቀቱን ማሸነፍ የቻለችው።

በ2025ቱ የአልትራማሮትን ውድድር እንድትሳተፍ ቤተሰቧና የአካባቢው ማህበረሰብ ናቸው ያበረታቷት።

ታዲያ የ30 አመቷ ሪቫስ ውድድሩን አሸንፋ ታሪክ ከሰራች በኋላ ድሉ የቤተሰቤ ነው ስትል ተናግራለች።

በምትኖርበት ማህበረሰብ ዘንድ ረጅም የእግር ጉዞ እና የአደን ውድድሮች የተለመዱ ናቸው።

ይህ በሜክሲኮ ቺሁዋሁዋ ክልል ውስጥ የሚገኘው የራራሙሪ ማህበረሰብ ዘንድ በስፋት የሚታወቅ በመሆኑ ራራሙሪዎች ለሩጫ የተወለዱ ናቸው በሚል ይነገራል።

በተራራማው ክፍል የሚኖሩት ራራሙሪዎች ምንም እንኳን ሥልጠናና ለሩጫ የሚሆን ዘመናዊ ትጥቅ ባይኖራቸውም ችግሮችን ተቋቁሞ ማለፍ በሚችለው አቅማቸውና ጥንካሬያቸው ምክንያት ከአትሌቶች ጋር ቢወዳደሩ እንኳ አሽናፊ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገለፃል።

ረጅም የእግር ጉዞ፣ አደንና መሰል ተግባራት በተራራማው ሥፍራ ለሚኖሩት ለራራሙሪ ማህበረሰብ የተለመደ ከመሆኑም በላይ፣ ከሀይማኖት ጋር የተያያዘና የማይሰበር መንፈሳዊ ጥንካሬን የሚያገኙበት መሆኑን የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ያመለክታል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review