ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ እያመረቱ የሚገኙ ፋብሪካዎችን ጎበኙ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በቬይትናም የቶዮ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ በነበረን ጉብኝት እና ከኩባንያው ፕሬዝደንቱ ጋር በነበረን ውይይት የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫዎችን በሀገራችን ለማምረት ተስማምተን ነበር።
ዛሬ በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በነበረን ጉብኝት በፓርኩ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጪያዎችን እያመረቱ በመመልከታችን ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል፡፡
ማምረቻው በከፍተኛ ጥራት ከፍተኛ ምርት የማምረት አቅም የተላበሰና በዘመናዊ የማሽን ሥርዓት የሚሰራ ሲሆን የምርት ውጤቱ ለማኑፋክቸሪንግ የውጪ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል።
ሁለት ተጨማሪ ማምረቻዎች በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ሲሆን ወደ ምርት የገባውን ማምረቻ ሥራ ሂደት ተመልክተናል። ይኽ ሥራ እሴት የተጨመረባቸው እና ያስቀመጥናቸውን ግቦች እና ፖሊሲዎች የሚያሳኩ ጨዋታ ቀያሪ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ከሚያደርገው የኢንቨስትመንት ስትራቴጂያችን ጋር የተጣጣመ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡