ትራምፕ በዩክሬን ጉዳይ ከፑቲን ጋር ለመምከር ወደ አላስካ አቀኑ

You are currently viewing ትራምፕ በዩክሬን ጉዳይ ከፑቲን ጋር ለመምከር ወደ አላስካ አቀኑ

AMN- ነሐሴ 9/2017 ዓ.ም

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን ጉዳይ ከሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመምከር ወደ አላስካ አቅንተዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሀገራቱን ለማሸማገል የሀገሪቱን ከፍተኛ ባለስልጣናት ያካተተ ልዑክ ይዘው ማቅናታቸው ተጠቁሟል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ ስኮት ቤሴንት፣ የንግድ ሚኒስትሩ ሆዋርድ ሉትኒክ እና ልዩ መልእክተኛው ስቲቭ ዊትኮቭን ጨምሮ 16 ባለስልጣናት በልዑኩ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ፣ እሳቸውን ያላካተተ ውይይት ውጤት እንደማያስገኝ መግለፃቸውን ዘገባው አስታውሷል።

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review