የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ2025/26 የውድድር ዓመት ዛሬ ምሽት በአንፊልድ ሲጀመር ባለሜዳው ሊቨርፑል ቦርንማውዝን 4ለ2 አሸንፏል ።
ከጨዋታው በፊት ሐምሌ ወር ላይ በመኪና አደጋ ሕይወቱ ላለፈው ዲያጎ ጆታ እና ወንድሙ አንድሬ የህሊና ፀሎት ተደርጓል ።
የሊቨርፑል ደጋፊዎችም በልዩ ስሜት ዘክረውታል ።
ለሊቨርፑል የማሸነፊያ ግቦቹን ሁጎ ኢኪቲኬ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ፌድሪኮ ኪዬሳ እና ሞሀመድ ሳላህ አስቆጥረዋል ። ሳላህ በመክፈቻ ጨዋታ ያስቆጠራቸውን ግቦች 10 አድርሷል ።
ለቦርንማውዝ ሁለቱንም ግቦች አንቷን ሴሜንዮ ከመረብ አሳርፏል ።
ሊቨርፑል ምንም እንኳን በቦርንማውዝ ቢፈተንም የውድድር ዓመቱን ሦስት ነጥብ በማግኘት ጀምሯል ።
ሸዋንግዛው ግርማ