ተስፋ የተጣለበት የሁለቱ መሪዎች ውይይት ያለበቂ ስምምነት ተቋጨ

You are currently viewing ተስፋ የተጣለበት የሁለቱ መሪዎች ውይይት ያለበቂ ስምምነት ተቋጨ

AMN-ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም

ሲጠበቅ የነበረው የአላስካው ውይይት ያለበቂ ስምምነት ተቋጭቷል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የራሺያ አቻቸው ቪላድሚር ፑቲን በሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ጉዳዮች እና በራሺያ-ዩክሬን ግጭት ዘላቂ መፍተሄ ዙሪያ በአላስካ ተገናኝተው መክረዋል።

ሶሰት ሰዓታትን ከፈጀው ውይይት በኋላ መሪዎቹ የጋራ መግለጫም ሰጥተዋል።

ፕሬዚደንት ትራምፕ በተለይ በራሺያ-ዩክሬን የሰላም ጉዳይ ላይ በተደረገው ውይይቱ ምንም አይነት ስምምነት ላይ አለመደረሱን ነገር ግን የተሻሻለ እና ተስፋ ሰጪ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ፑቲን በበኩላቸው ከዩክሬን ጋር የገቡበትን ግጭት ለማስቆም “ከልብ ፍላጎት አለኝ” ቢሉም ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮችን አልሰጡም። መሪዎቹ በቀጣይ ምናልባትም በሞስኮ ሊገናኙ እንደሚችሉ ፑቲን በመግለጫቸው ፍንጭ ሰጥተዋል።

ሁለቱ መሪዎች በጋራ ከሰጡት መግለጫ ውጪ የጋዜጠኞችን ጥያቄ ከማስተናገድም ተቆጥበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review