የህዳሴው ግድብ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ከደለል ለመታደግ ከፍተኛ አስተዎፅኦእንዳለዉ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች የጥናትና ምርምር አማካሪ አቶ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ ገለጹ

You are currently viewing የህዳሴው ግድብ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ከደለል ለመታደግ ከፍተኛ አስተዎፅኦእንዳለዉ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞች የጥናትና ምርምር አማካሪ አቶ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ ገለጹ
  • Post category:ልማት

‎AMN-ነሀሴ 10 /2017 ዓ.ም

‎የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከመጀመሩ በፊት ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በዓባይ ወንዝ ላይ አንድ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በጋራ ለመገንባት በአንድ የፈረንሳይ ኩባንያ ማስጠናታቸውን ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ድጅታል ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ አንስተዋል።

‎ይሁን እንጅ በወቅቱ ለመገንባት የታቀደው ፕሮጀክት ሳይሳካ መቅረቱን ነው የጠቆሙት።

‎በመቀጠልም በሌላ ጊዜ 3ቱ ሀገራት ከባሮአኮቦ፣ ተከዜና አባይ ተፋሰስ መካከል በአንዱ ተፋሰስ ግዙፍ የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ለመገንባት በጋራ አጥንተው በጋራ ለማልማት ተስማምተው እንደነበር አስታውሰዋል።

‎በኋላም ከ3ቱ ተፋሰሶች መካከል የግድብ ፕሮጀክቱ በዓባይ ተፋሰስ ላይ እንዲገነባ ሀገራቱ የጋራ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ነው አቶ ፈቅ አሕመድ የተናገሩት።

‎ኢትዮጵያ በወቅቱ በዓባይ ተፋሰስ የሚገኙትን የቤቋቦ፣ መንዳያ እና ቦርደር የተባሉ ቦታዎችን ለግንባታ ምቹ መኾናቸውን በዕጩነት ማቅረቧን ጠቁመዋል።

‎ግብጽና ሱዳንም ኢትዮጵያ በእጩነት ካቀረበቻቸው 3ቱ የዓባይ ተፋሰሶች መካከል አንዱ በኾነው “ቦርደር ዳም” ላይ እንዲገነባ ጽኑ ፍላጎት እንደነበራቸው አንስተዋል።

‎”ቦርደር ዳም” አሁን ላይ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የተገነበባበት ቦታ መጠሪያ ሥም ነው።

‎አቶ ፈቅ አሕመድ ግብጽና ሱዳን ግድቡ “ቦርደር” ከተባለው ቦታ ላይ እንዲገነባ የፈለጉበትን ሦሥት መሠረታዊ ምክንያቶችን ጠቁመዋል።

‎የመጀመሪያው ደለል ለማግኘት ነው ። ሁለተኛው ከጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ለመዳን ሲኾን የመጨረሻው ያለምንም ወጭ ከግድቦቻቸው የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ተጠቃሚ ለመኾን ነው ብለዋል።

‎አቶ ፈቅ አሕመድ እንደገለጹት፣ አባይ ወደ ሱዳን ሲፈስ ከፍተኛ ጉልበት ስላለው ሱዳንን በጎርፍ አደጋ የማጥለቅለቅ አቅም አለው። ሀገሪቱ በጎርፍ መጥለቅለቅ በየዓመቱ ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዋ ቀውሶች ትዳረጋለች። በየዓመቱ በጎርፍ አደጋ ብቻ እሰከ 60 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ይደርስባታል።

‎የተፋሰሱ ሀገራት ባለፉት ጊዚያት የደለል ክምችት ጥቅም እንዳለው ይረዱ እንጅ አሁን ላይ ፈጽመው ደለሉን እንደማይፈልጉም አማካሪው ተናግረዋል ።

‎ከዓባይ ተፋሰስ የሚወርደው ከፍተኛ የኾነ ደለል የግብፅን “አስዋን” ግድብ እየሞላ ግብጽን ላልተፈለገ ወጭ እየዳረጋት መኾኑን ነው የገለጹት።

‎በተመሳሳይ ደለሉ የሱዳንን ግድቦች፣ ቦዮችን እና የእርሻ መሬቶችን ሳይቀር እየሞላ ለከፋ ችግር እየዳረገ ነው ብለዋል። ሁለቱ ሀገራት ከአባይ ደለል ኪሳራ እንጅ ትርፍ የላቸውም ብለዋል። እነዚህ ሀገራት ደለሉን ለማውጣት ብቻ በየዓመቱ እሰከ መቶ ሚሊዮን ዶላር ወጭ እንደሚያደርጉ ነው ያነሱ።

‎ግብጽና ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ያስጠኑትን ፕሮጀክት በጋራ ለማልማት ፍላጎታቸውን ቢያሳዩም በጅኦፖለቲካዊ ምክንያት መገንባት አልቻሉም።

‎ኢትዮጵያም ግን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ቀደም ሲል ግብጽና ሱዳን በፈለጉት ቦታ መገንባት ችላለች።

‎ይህም ለሁለቱ ሀገራት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታን አስገኝቷል። በተለይም ከጎርፍ አደጋ እንዲድኑ አድርጓቸዋል፤ ግዶቦቻቸው በደለል እንዳይሞሉ አስችሏቸዋል፤ ከግድቦቻቸው በሚሞላው ውኃም ንጹህ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ኾኗል ብለዋል።

‎ኢትዮጵያ ያለማንም እርዳታና ብድር በራሷ ላብ እና ወጪ የገነባችው የህዳሴ ግድብ ጠቀሜታው ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይኾን የተፋሰሱን ሀገራት ፍላጎትና ብሔራዊ ጥቅም ያከበረ ነው ተብሏል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review